Dogma of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church in this channel; Canonical and traditional teachings are transmitted. For comments: suggestions and questions, contact us here ☞@Ethiopian_Orthodox_botBuy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
This channel is part of the discussion
የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች appears in 5 event pages on TGScope፬. ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት በሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ የአማኑኤልን ምሥጢር አየና አሰምቶ ተናገረ፡፡ አማኑኤል ማለት ሰው የኾነ አምላክ ማለት ነውና “ሕፃን ተወለደልን፤ ወልድ ለሕማም ለሞት ተሰጠልን፡፡ አንድም ወልድ ለኩነተ ሥጋ ተሰጠልን ፤ ሕጻንም ኾኖ ተወለደልን” ብሎም ጮኸ /ኢሳ.፱፡፮/፡፡ አትናቴዎስ ሐዋርያዊም “ስለ ድኅነተ ሰብእ የአዳምን ባሕርይ ገንዘብ አደረገ፤ ካሣ ይከፍልልን ዘንድ ቃል ሥጋ ኾነ” ይላል /Ep. 61:3./፡፡…
ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ ወደርሱ መጣ ከእርሱም ጋራ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ የከበሩ ነቢያትና ሐዋርያት ሁሉም ሰማዕታትና ጻድቃን የጳጳሳት አለቆች የመላእክት አለቆችም ከሠራዊቶቻቸው ጋራ አሉ። መድኃኒታችንም እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ አንተ በመከራዬ መሰልከኝ እኔም በመንግሥቴ ከእኔ ጋራ እንድትመስለኝ አደርግሃለሁ። እነሆ የዚህ ዓለም ድካምህ ተፈጸመልህ በእኔ ዘንድም የምቀበለው ሆነ ከእንግዲህስ…
ጳጉሜ/ጳጉሜን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከነሐሴ በኋላ ጳጉሜን የምትባል አምስት ቀን አለች፡፡ ወር እንዳትባል አቅም ያንሳታል፡፡ ሳምንት እንዳትባል አምስት ቀን ብቻ ኾናለች፡፡ ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ ግን “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ መኾኑ በአበው ቃል ተነግሯል፡፡ “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው ፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ…
‹‹ዑራኤል የተባለ መላእክ ሊረዳኝ መጣ›› (ዕዝ.ሱቱ ፪፥፩) በነገደ መላእክት ከተሾሙት ሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ቅዱስ ዑራኤል የቅዳሴ ቤቱ የሚከበርበትና ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል የዕውቀትን ጽዋ ያጠጣበት ዕለት ሐምሌ ፳፪ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ በመከራ ጊዜ ረዳት የሆነው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤል በዘመናት ለነገሡ የሀገራችን ነገሥታት ያደረገውም ውለታ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለ ንዋየ ማርያም…
የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅም በዚህ በጨረሻው ሀሳብ ይስማማል፡፡ ሰማያዊ ክብርን የሚያስገኝ አኩሪ ገድል በመፈጸም የቤተክርስቲያን ታላቅ አለኝታ አባትና መሪ የሆኑት የዘመናችንን ታላቅ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስን ትውልዱ የግድ ሊያስባቸውና ሊዘክራቸው ይገባል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (united nations) አቡነ ዼጥሮስን "የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት" ወይም በፈረንጅኛው አፍ (MARTYR OF THE MILLENIUM) በሚል መጠሪያ…