📌 የMarvin Gaye አሳዛኝ ታሪክ
ከ45ኛ የልደት ቀኑ በፊት… አባቱ ራሱ ልጁን ገ*ደ*ለ*ው።
🎯 April 1, 1984 — Los Angeles, California
ስሙ Marvin Gaye ነበር።
🎙️ ዘፋኝ፣
✍️ የሙዚቃ ጸሐፊ፣
🎹 ፕሮዲዩሰር፣
በSoul እና R&B ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ ስም።
“Prince of Motown” ተብሎም ይጠራ ነበር።
Marvin Pentz Gay Jr. በApril 2, 1939 በWashington, D.C. ተወለደ። ያደገበት ቤት ግን በፍቅርና በሰላም የተሞላ ቤት አልነበረም።
አባቱ ጥብቅና ሃይማኖተኛ ሰው ቢሆንም፣ በቤቱ ውስጥ የነበረው ግጭትና ጥቃት የMarvinን የልጅነት ህይወት የተዘበራረቀ ነበር
ይህ ሰው ከዚያ ሁሉ ችግር ለመውጣት የሚያውቀውን አንድ መንገድ መረጠ፤ ሙዚቃ። 🎶
በ1961 ከዶ-ዋፕ ቡድኖች እና ከSession drummer ስራዎች በኋላ ወደ Motown Records ገባ። ከታላቁ የMotown መስራች Berry Gordy ጋርም ሰራ።
ነገር ግን Marvin በቀላሉ የሌሎችን ፎርሙላ የሚከተል አርቲስት አልነበረም።
ሙዚቃው ከፍቅር በላይ ነበር።
ስለ ጦርነት ይፍን ነበር።
ስለ ድህነት ይዘፍን ነበር።
ስለ ማህበረሰብ ችግሮች፣ ስለ ሰው ልጅ ህይወትና ስለ ፍቅርም ይዘፍን ነበር።
🎵 “What’s Going On” የሚለው ዘፈኑ በVietnam War እና በማህበራዊ ችግሮች ዙሪያ ያለውን ስሜት ለአንድ ትውልድ ድምጽ ሆኖ ተናገረ።
እንዲሁም “Sexual Healing” የሚለው ዘፈን ዓለም አቀፍ ተወዳጅነት አመጣለት።
Jazz፣ Gospel፣ Funk እና Soulን በራሱ ልዩ መንገድ በማዋሃድ የሚታወቅበትን የሙዚቃ ዘይቤ ፈጠረ።
ነገር ግን ከዓለም ፊት የሚታየው Marvin እና በውስጡ የሚዋጋው Marvin ሁለት የተለያዩ ሰዎች ይመስሉ ነበር።
የልጅነት ጉዳት፣ የቤተሰብ ግጭት፣ የግል ችግሮች፣ የመድረክ ፍርሃት እና የሱስ ችግሮች ህይወቱን አስቸጋሪ አደረጉት።
እውነቱ ግን በሙዚቃ ዓለም ላይ ትልቅ ሰው ሆኖ ሳለ፣ በግል ህይወቱ የራሱን ቅጥ ያጣ ችግር እየተዋጋ ነበር።
💔 ከሞቱ በፊት የነበሩት ሰዓታት
April 1, 1984።
ይህ ቀን ከ45ኛ የልደት ቀኑ አንድ ቀን ብቻ ይቀረው ነበር።
በLos Angeles ቤተሰቡ ቤት ውስጥ በእናቱና በአባቱ መካከል ክርክር ተነሳ። ጉዳዩ የጠፋ የInsurance ሰነድ እንደነበር ተዘግቧል።
ክርክሩ እየተባባሰ ሲሄድ Marvin እናቱን ለመጠበቅ ጣልቃ ገባ።
ከዚያ አባቱ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ።
እና ከዚያ… Marvin ራሱ ለአባቱ የሰጠውን .38 caliber Smith & Wesson ሽጉጥ ይዞ ወጣ።
Marvin በአባቱ ተኩሶ ተመታ።
እንደ ሪፖርቶች ከሆነ ሁለት ጥይቶች ተመተውት ህይወቱ አለፈ።
44 ዓመቱ ነበር።
በልደቱ በፊት አንድ ቀን።
ከዓለም አቀፍ የሙዚቃ ኮከብነት ወደ ሞት።
እና በጣም አሳዛኙ ነገር?
የህይወቱን መጨረሻ ያመጣው ሽጉጥ ለአባቱ የገዛው እሱ ራሱ ነበር።
የMarvin Gaye ሞት የሙዚቃ ዓለምን አስደነገጠ።
እሱ ብቻ አልሞተም፤ በአንድ ትውልድ ውስጥ ድምጽ የሆነ ሰው በድንገት ጠፋ።
ዛሬም “What’s Going On” ስንሰማ፣ የእሱን ድምጽ ብቻ አንሰማም።
የጦርነት፣ የድህነት፣ የፍቅር፣ የቤተሰብ ጉዳት እና የሰው ልጅ ትግል ታሪክ እንሰማለን።
Marvin Gaye ከሞተ ከ40 ዓመታት በላይ ቢሆንም፣ ተፅዕኖው አልሞተም።
🎶 ዘፈኖቹ አሉ።
🎶 ድምፁ አለ።
🎶 ታሪኩ አለ።
🎶 ተፅዕኖውም ዛሬም በR&B እና Soul ሙዚቃ ውስጥ ይታያል።
Marvin Gaye — ከዓለም የተሰማ ድምፅ፣ ግን በግል ህይወቱ የራሱን ጦርነት ማሸነፍ ያልቻለ ሰው።
🕊️ Rest in Peace, Marvin Gaye.
👇👇👇ተወዳጁን ሙዚቃ SEXUAL HEALING
commit section ላይ አለ