CountryEthiopiaAugust 2026

Ethiopia — August 2026

What Telegram channels wrote about Ethiopia in August 2026: 922 posts from 210 channels, collected automatically from public Telegram channels.

922 posts·210 channels

More posts — page 26

922 posts total

በክልሉ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች ውጤታማነትን እያሳደጉ ነው

ቡታጅራ፤ ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች የኢንዱስትሪውን ውጤታማነት ይበልጥ እያሳደገው መሆኑ ተገለጸ።

የክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ312 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ኢንዱስትሪዎች በቡታጅራ ከተማ ያስገነባቸውን የማምረቻ ሼዶች ዛሬ አስረክቧል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ናትናኤል ሚሊዮን በዚሁ ወቅት፣ ኮርፖሬሽኑ የአምራች ኢንዱስትሪውን ውጤታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ከማበረታታት ባለፈ የመስሪያና የመሸጫ ሼዶችን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ተደራሽነትን በማስፋፋት ለሥራቸው ምቹ ሁኔታ እየፈጠረም ይገኛል።

በዚህም በዘርፉ የተሰማሩ የግል ባለሀብቱን እና ሥራ አጥ ዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ገልጸው፣ ከውጭ የሚገባ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካትም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ተችሏል ብለዋል።

Source: Ethiopian News Agency Economy @Ethiopianbusinessdaily

Ethiopia is preparing to rewrite three of its core intellectual property laws, some of which were drafted before smartphones, mobile money and the digital economy existed.

SignalThe Ethiopian Intellectual Property Authority is reportedly preparing to amend three legal instruments at once: the laws governing minor inventions and industrial designs, trademarks, and copyright.

The Authority's public relations and communications executive, gave two reasons to a local media outlet last week.

The statutes are more than two decades old, and the country is preparing for membership of the World Trade Organization.Both reasons are sound.

The first is also a little modest.

123/1995, which covers patents, utility models and industrial designs, is thirty-one years old, making it older than the median Ethiopian.

Read More

Source: Shega Media Ethiopia @Ethiopianbusinessdaily

ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ። •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• ነሀሴ 5 /2018 ዓ.ል| ሰፈር 28 /1448 ዓ.ሒ بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ •••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••• አዲስ አበባ |

​የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ መከተ ሙሄን እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልመናን መሐመድን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

​ውይይቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን የሥራ ግንኙነትና ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን በተለይም ለህዝበ ሙስሊሙ የሚሰጡ የፍትህና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ ማድረግ በሚቻልባቸው ተቋማዊ አሰራሮች ዙሪያ ሰፊ ጊዜ ወስደው መክረዋል።

ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ማጎልበትና የጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የ​ክቡር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በሁለቱ ተቋማት መካከል የሚደረግ የጠበቀ አጋርነት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት እና ለፍትህ መስፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በአጽንኦት አንስተዋል።

የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ መከተ ሙሄ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው የተሻለ አገልግሎት በመሰረጠት የህዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት ለማሟላት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በውይይቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን፣ ምክትል ፕሬዝደንት ሸይኽ ጁነይድ ሐምዛ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። •••••••••••••••••••••••••••••••••••••• የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት ይከታተሉን | Follow us፡ ቨቨዠፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council ቴሌግራም | t.me/eiasc1 ትዊተር | https://x.com/eiasc1

Aug 11, 10:21 AMMore from @eiasc1

የ ኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን 22   ክፍት የሥራ ቦታዎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አውጥቷል

👉 የስራ ቦታ አዲስ አበባ 👉የቅጥር ሁኔታ በቋሚ በዝውውር እና በኮንትራት

በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሱት የትምህርት መስኮች  👇👇👇👇 ሆርቲካልቸር፣ አግሮኖሚ፣ የዕፅዋት ማዳቀል፣ የዘር ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የዕፅዋት ፓቶሎጂ፣ አግሮ ኢኮኖሚክስ፣ አፕላይድ ባዮሎጂ፣ የዕፅዋት ሳይንስ፣ ኬሚስትሪ፣ አናሊቲካል ኬሚስትሪ፣ ምግብ ሳይንስ፣ ፕላንት ሳይንስ፣ ኢትዮሞሎጂ፣ ኔማቶሎጂ፣ ባዮቴክኖሎጂ፣ አግሪካልቸራል ባዮቴክኖሎጂ፣ ሰፕላይ ማኔጅመንት፣ ፕሮጀክት ማኔጅመንት፣ ማኔጅመንት፣ ቢዝነስ ማኔጅመንት፣ አካውንቲንግ፣ ማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ አውዲዮቪዥዋል፣ ፎቶግራፊ፣ ሲኒማቶግራፊ፣ ቪዲዮግራፊ፣ ጆርናሊዝም፣ ኮሙኒኬሽን፣ አውቶሞቲቭ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ኤሌክትሪሲቲ፣ የግብርና መሀንዲስነት፣ ማሽነሪ መሀንዲስነት፣ የግብርና መካናይዜሽን መሀንዲስነት፣ አግሪካልቸራል ኢንጂነሪንግ፣ መልካም አስተዳደር፣ ፖሊሲ አናሊስስ፣ ስትራቴጂክ ማኔጅመንት፣ ፖለቲካል ሳይንስ፣ አለም አቀፍ ግንኙነት፣ ፐብሊክ አድሚኒስትሬሽን፣ ኢኮኖሚክስ፣ የህግ ትምህርት፣ ሀርድዌር እና ኔትወርክ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ሲስተም፣ ሎጂስቲክስ።

በነዚህ የትምህርት መስኮች የተመረቃቹ አሁኑኑ አመልክቱ

👉ስራ ለሚፈልጉ ጓደኞቻቹ ሼር አድርጓቸው

ዝርዝር የስራዎቹን መረጃ ለማየት እና በኦላይን ለማመልከት ከታች ሊንኩን ይጫኑ👇👇👇👇👇👇

https://ethiopianjobs.et/jobs-in-ethiopia-ethiopian-agricultural-authority-job-vacancy-2026/

Global Bank Ethiopia S.C -Vacancy Announcement Global Bank Ethiopia S.C would like to invites competent and interested candidates for the following position. Position 1: Head, Social Media Section Position 2: Sales Division Head How to Apply: (ይመልከቱ፤ ፈጥነው ያመልክቱ!) For details use the link below and apply: 👇👇👇 https://sewaseweth.com/global-bank-ethiopia-s-c-job-2/ Deadline: August 14, 2026 🔗መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ እባክዎ ለወዳጅ-ጓደኛዎ ያጋሩት Don’t forget to share for your friends

BGI Ethiopia  -Vacancy Announcement BGI Ethiopia  would like to invites competent and interested candidates for the following position. Position: Jr. Utility Operator How to Apply: (ይመልከቱ፤ ፈጥነው ያመልክቱ!) For details use the link below and apply: 👇👇👇 https://sewaseweth.com/bgi-ethiopia-job-23/ Deadline: August 15, 2026 🔗መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ እባክዎ ለወዳጅ-ጓደኛዎ ያጋሩት Don’t forget to share for your friends

Ethiopian Pulses, Oilseeds and Spices Processors and Exporters Association (EPOSPEA) -Vacancy Announcement Ethiopian Pulses, Oilseeds and Spices Processors and Exporters Association (EPOSPEA) would like to invites competent and interested candidates for the following position. Position 1: External Audit & Financial Review Services Position 2: Internal Financial Controller Position 3: Senior Finance Officer  Position 4: General Manager (GM) Position 5: IT Officer How to Apply: (ይመልከቱ፤ ፈጥነው ያመልክቱ!) For details use the link below and apply👇👇👇 https://sewaseweth.com/ethiopian-pulses-oilseeds-and-spices-processors-and-exporters-association-job/ Deadline: August 28, 2026 🔗መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ እባክዎ ለወዳጅ-ጓደኛዎ ያጋሩት Don’t forget to share for your friends

በሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት  ዙሪያ ሥልጠና እየተሰጠ ነው ……///……. በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እና ሪጅኖች ለተመደቡ የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና አስተባባሪ መሐንዲሶች በሥራ ላይ ደህንነት ላይ ያተኮረ ሥልጠና መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ ላይ ደህንነትና ጤና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ ኮርሳ ተሬሳ እንደገለፁት ሥልጠናው መሐንዲሶቹ በተመደቡባቸው የሥራ ቦታዎች ላይ በሚኖራቸው የሥራ ላይ ደህንነት እና ጤንነት ክትትልና ቁጥጥር ላይ ያላቸውን የማስፈፀም አቅም ለማሳደግ ያለመ ነው።

ሥልጠናው ባለሙያዎቹ በሥራ ላይ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ስጋቶችን በመለየት መከላከል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን  ነው የገለፁት።

ተጨማሪ ለማንበብ… https://www.eep.com.et/?amh-news=በሥራ-ላይ-ደህንነት-እና-ጤንነት-ዙሪያ-ሥ&lang=am

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ አስገኝቷል

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 4 /2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ አስገኝቷል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ ነው ብለዋል።

በዚህም ይህ ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል ነው ያሉት።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎችና ጎብኝዎች የሚገናኙበት ሥፍራ መሆን ችሏል።

ከቤተሰቦችና ሕፃናት፣ከስፖርት ቡድኖችና ከሠርግ ተካፋዮች ጀምሮ እስከ ዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች፣ እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በቦታው ይገኙበታል።

Source: Ethiopian News Agency Economy @Ethiopianbusinessdaily

በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው

በኢትዮጵያ በውርስና ስጦታ ላይ አዲስ ታክስ ሊጣል ነው በኢትዮጵያ በውርስ ወይም በስጦታ በሚገኙ ገቢዎች ላይ አዲስ የታክስ ዓይነት ሊጣል መሆኑ ተገለጸ።

ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆኑ የውርስና የስጦታ ገቢዎች ለዚህ ታክስ እንደሚዳረጉ ተመልክቷል።

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) የአምስተኛውን ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም ግምገማ ተከተሎ ይፋ ባደረገው ባለ 132 ገጽ ሙሉ ሪፖርት እንደጠቆመው፣ የአገሪቱ የታክስ መሠረት በጣም ጠባብ በመሆኑ መንግሥት በየዓመቱ የአገር ውስጥ ገቢውን ለማሳደግ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችን ለመተግበር አቅዷል።

በዚሁ ሪፖርት መሠረት በውርስና ስጦታ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በሚገኝ ገቢ ላይ ታክስ ይጣላል።

በሲጋራ፣ በአልኮልና በነዳጅ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታክስ እንደሚጨምር የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም አገራዊ ገቢን ከመጨመር ባለፈ ለጤና ፖሊሲዎች አተገባበር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተመልክቷል።

Source: Ethio FM 107.8 @Ethiopianbusinessdaily

🌼🌼 ከ 800 በላይ ስራዎች ረፖርተር ጆብስ ( Reporter Jobs ) website ለይ ማግኘት ይችላሉ !!

🌼🌼  አሁኑኑ በፈለጉት አማራጭ ገብተው ያመልክቱ

🌟 አዲሱ ስራዎን በቀላሉ ያግኙ !

የረፖርተር  ስራዎችን በእነዚህ አማራጮች ማግኘት ይችላሉ፦

💯 Website: www.ethiopianreporterjobs.com 💯 Facebook: http://bit.ly/2mPD7EG 💯 Telegram: https://bit.ly/3exwhdn 💯 Linkedin: https://bit.ly/2XJzm45 💯 Twitter: https://bit.ly/3cuJTnF 💯 Instagram: https://bit.ly/3fCE5j1

ይጎብኙን፤ ይከተሉን፤ ላይክ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን።

⛔️⛔️በዚህ ሳምንት የወጡ ስራዎች

::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••::

⛔️⛔️በዚህ ሳምንት የወጡ ስራዎች በ ስራ ቦታ

✅በ አዲስ አበባ የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3rYVB41 ✅በ አማራ ክልል የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3ErEGOI ✅በ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3NW1ucf ✅በ ሶማሌ ክልል የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3NRuYrK ✅በ ኦሮሚያ ክልል የወጡ ስራዎች   https://bit.ly/3RG13mA ✅በ ደቡብ ክልል የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3SLjZB6 ✅በ አፋር ክልል የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3TjYGa4 ✅በ ትግራይ ክልል የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3GUBlHM ✅በ ድሬደዋ የወጡ ስራዎች https://bit.ly/3hgQA4H ✅ Project based የሆኑ https://bit.ly/3fHiEx4

::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••::

::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••::

💢 ከታች በተዘረዘሩት የሥራ ዘርፎች በተማሩበት መስክ ወይም የሙያ ስብጥር የሥራ ማስታወቂያዎችን ለማየት አንዲሁም ለማመልከት ሊንኮቹን ይጠቀሙ

✅Banking & Insurance  https://bit.ly/3xcxEKf ✅Finance & Accounting  https://bit.ly/3rfkkkp ✅NGO  https://bit.ly/3rdSNQq ✅Management  https://bit.ly/3v8JmTg ✅Economics  https://bit.ly/35XZJK6 ✅Public Relations https://bit.ly/37w1EWs ✅Nursing  https://bit.ly/3xvqVeH ✅Civil Engineering  https://bit.ly/3v4Jrrp ✅Electrical Engineering  https://bit.ly/3JomG6W ✅Mechanical Engineering  https://bit.ly/3JomG6W ✅Chemical Engineering  https://bit.ly/3JomG6W ✅Industrial Engineering  https://bit.ly/3JomG6W ✅Textile Engineering  https://bit.ly/3JomG6W ✅Hydraulics Engineering  https://bit.ly/3JomG6W ✅Food Engineering  https://bit.ly/3JomG6W ✅Const. & Architecture  https://bit.ly/3v4Jrrp ✅Insurance  https://bit.ly/3xcxEKf ✅IT & Telecom  https://bit.ly/35Ulpqj ✅Graphics Design  https://bit.ly/3rNxR30 ✅Hotel & Hospitality  https://bit.ly/3DVh6Yl ✅Healthcare  https://bit.ly/3xvqVeH ✅Agriculture  https://bit.ly/3KCZWBe ✅Driver  https://bit.ly/37z1rli ✅Legal  https://bit.ly/3LWVv4R ✅Language  https://bit.ly/3reDSoW ✅Business and Administration  https://bit.ly/3LNR3oM ✅Admin/Clerical & Secretarial  https://bit.ly/37tKgBN ✅Automotive, Machinery & Mechanic  https://bit.ly/3v7yqW2 ✅Logistics & Transportation  https://bit.ly/37z1rli ✅Advertising/Media & Journalism  https://bit.ly/3jjwvbJ ✅Education & Training  https://bit.ly/3NWVpfg ✅Human Resource  https://bit.ly/3re6jTX ✅Statistics  https://bit.ly/3Jp0xoQ ✅Pharmaceutical  https://bit.ly/35TZn74 ✅Travel & Tourism  https://bit.ly/3rd4nLB ✅Community & Social Science  https://bit.ly/37w1EWs ✅Customer Service & Support  https://bit.ly/3jmFngI ✅Program & Project Management  https://bit.ly/3DVikTr ✅Security  https://bit.ly/3DTkQtD ✅Cleaning  https://bit.ly/3uniwYu ✅Cook/Chef  https://bit.ly/3uniwYu ✅Supply Chain, Procurement & Purchasing  https://bit.ly/3NYu3W4 ✅Maintenance, Skilled Labor & Manufacturing  https://bit.ly/3uniwYu ✅Machine Operators https://bit.ly/3uniwYu ✅Environment & Natural Resource https://bit.ly/3EukR9n ✅Research & Science https://bit.ly/3Jp0xoQ

::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••:: 💯 Don't forget to share/ወዳጅ ዘመድዎ እንዲደርሰው ሼር ያድርጉ ::•••••™ ✿::✿:: ✿::✿:: ✿™•••••::🌼🌼 ከ 800 በላይ ስራዎች ረፖርተር ጆብስ ( Reporter Jobs ) website ለይ ማግኘት ይችላሉ !!

🌼🌼  አሁኑኑ በፈለጉት አማራጭ ገብተው ያመልክቱ

🌟 አዲሱ ስራዎን በቀላሉ ያግኙ !

የረፖርተር  ስራዎችን በእነዚህ አማራጮች ማግኘት ይችላሉ፦

💯 Website: www.ethiopianreporterjobs.com 💯 Facebook: http://bit.ly/2mPD7EG 💯 Telegram: https://bit.ly/3exwhdn 💯 Linkedin: https://bit.ly/2XJzm45 💯 Twitter: https://bit.ly/3cuJTnF 💯 Instagram: https://bit.ly/3fCE5j1

A deep listening session featuring A Rush to Nowhere, the second album by Ethiopian-American artist Arima Ederra, is scheduled for 20 August from 7:00 PM to 9:00 PM at the Social Addis Rooftop. The listening session will be followed by a video Q&A session with the artist, offering attendees an opportunity to engage directly with the work and its themes.

​This phone-free gathering aims to provide a focused listening environment, with herbal tea served to attendees throughout the evening.

Location: Social Addis, Bole Atlas

@linkupaddis

Aug 11, 08:01 AMMore from @linkupaddis

🚨 NEW JOB ALERT!

💼 Job Title: Administrative Assistant 💸 Salary: 5,000 Net Monthly + transport allowance ✅️ Applicants Needed: 1 Vacancy 🌍 Job Type: Full Time - Onsite 📂 Experience: 0-1 Years 📍 Location: Bole Bulbula Addis Ababa, Ethiopia

📂 Job Overview: Private is seeking a highly organized, trustworthy, proactive, and detail-oriented Administrative Assistant to work directly under the CEO and support the effective management of the company's daily administrative and operational activities. The ideal candidate will help the brand by monitoring and coordinating employee time and attendance, company materials and resources, financial inflows and outflows, client communication, schedules, documentation, and administrative activities. You will collaborate across operations to serve as an important coordination point between the CEO, employees, clients, suppliers, and other stakeholders. We recommend clicking the link at the bottom of this text to read the full details of the job and apply.

📂 Qualifications: • Education: Diploma or Bachelor's degree in Management, Business Administration, Accounting, Finance, Office Administration, or a related field • Experience: 0–2 years of relevant administrative, office, operations, finance-support, or executive-assistant experience is preferred • Technical Skills: Good knowledge of Microsoft Office, particularly Excel, Word, and PowerPoint, with knowledge of Google Workspace as an advantage • Core Insight: Good numerical and record-keeping skills, and experience handling administrative or financial records is an advantage • Soft Skills: Good written and verbal communication skills, strong organizational and time-management abilities, active listening, adaptability, and collaboration • Key Responsibilities: Monitor employee attendance, working hours, lateness, absences, leave, and overtime. Monitor the availability and use of company materials, office supplies, equipment, and other resources. Maintain accurate records of money coming into and going out of the company, and record daily, weekly, and monthly financial transactions. Provide direct administrative support to the CEO and follow up on assigned tasks and decisions. Make phone calls and follow up with clients regarding appointments, payments, documents, and other administrative matters. • Openings: 1 Vacancy

🏢 PRIVATE CLIENT✅ ⭐️ Status: Verified individual✅️ 🔔 Deadline: Aug 25, 2026 🔗 CLICK FOR DETAILS & APPLY

Aug 11, 06:29 AMMore from @fetroader

የኃይል መቋረጥን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የብረት ምሰሶዎች 🏗   በኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ድንገተኛ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት ፈጣን መልሶ ጥገና ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ የአደጋ ጊዜ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች (Emergency Restoration Towers) በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ተደርገዋል።   ይህ ቴክኖሎጂ ምን ዓይነት ጥቅሞችን ይዞ መጥቷል?   ፈጣን መልሶ ጥገና  ቀደም ሲል በአደጋ ወቅት ከ18 እስከ 20 የሚደርሱ የእንጨት ምሶሶዎችን መትከል ይጠይቅ የነበረ ሲሆን አዲሶቹ ምሰሶዎች ግን በደጋፊ ገመዶች (Anchor Wire) በቀላሉ የሚገጣጠሙ በመሆናቸው የተቋረጠውን መስመር በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወደ ሥራ ለማስገባት ያስችላሉ።   የኃይል ጭነት ማመጣጠን የተጨናነቁ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን አነስተኛ የኃይል ፍሰት ወደሚገኝባቸው በማዘዋወር ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ አካባቢዎች በፍጥነት ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ያደርጋል።   የሠራተኞች ደህንነትና የአሰራር ዘመናዊነት የጥገና ሠራተኞችን ለጉዳት እንዳይጋለጡ በማድረግ ደህንነታቸውን አስተማማኝ ያደርጋል።   በተግባር ምን ውጤት ተገኘ? በሞጆ አካባቢ በተደረገ ሥልጠናና ልምምድ ባለሙያዎቹ የምሰሶ ተከላ ጊዜን ከግማሽ ቀን በታች ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡ በተጨማሪም ከቢሾፍቱ ወደ ቆቃ እና ሁርሶ እንዲሁም ከገላን ወደ ሞጆ በሚሄዱ ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመሮች ላይ ተከሰተው እስከ 7 ቀናት ሊወስዱ ይችሉ የነበሩ የኃይል መቋረጦችን በእነዚህ ምሰሶዎች አማካኝነት ፈጣን መፍትሔ መስጠት ተችሏል።   በቀጣይ ምን ታስቧል? ቴክኖሎጂውን ወደ ሁሉም ሪጅኖች ለማስፋትና የጥገና ምላሽ ጊዜን ይበልጥ ለመቀነስ የሚያስችሉ ዝግጅቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ።

💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

📌ፌስቡክ↠https://www.facebook.com/Ethioelectric 📌ቴሌግራም↠https://t.me/EEPCommuication 📌ሊንክዲን↠ https://www.linkedin.com/company/ethiopian-electric-power 📌ትዊተር↠https://twitter.com/EEPethiopia 📌ዩትዩብ↠https://www.youtube.com/@ethiopowermedia 📌ድረ- ገጽ ይጎብኙ https://www.eep.com.et ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም

ምስባክ ዘነሐሴ ፭ ዘቅዳሴ ፍልሰታ በድምጽ

መዝ ፲፯(17) ፥ ፵፫(43) "ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ። ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ። ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ።" "የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል። በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤"

@Ethiopian_Orthodox

🔔ዛሬ ምን ይቀደሳል?

የነሐሴ ፭(5) ግጻዌ መልእክታት 1. ፪ኛ ቆሮንቶስ ፲፪(12) ፥ ፲(10) - ፲፯(17) 2. ፩ኛ ዮሐንስ ፭(5) ፥ ፲፬(14) - ፍጻሜ 3. የሐዋርያት ሥራ ፲፭(15) ፥ ፩(1) - ፲፫(13)

ምስባክ መዝ ፲፯(17) ፥ ፵፫(43) "ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ። ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ። ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ።"

"የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል። በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤"

ወንጌል የሉቃስ ወንጌል ፲፭(15) ፥ ፩(1) - ፲፩(11) ፩ ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። ፪ ፈሪሳውያንና ጻፎችም። ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ። ፫ ይህንም ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል። ፬ መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው? ፭ ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤ ፮ ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ። የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል። ፯ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል። ፰ ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት? ፱ ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ። የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች። ፲ እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል። ፲፩ እንዲህም አለ። አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።"

ቅዳሴ ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) አው ዘሠለስቱ ምዕት (በግዕዝ ዜማ)።

@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

፲፬. እናትነትን ከአገልጋይነት ጋር /ሉቃ.፩፡፴፰/ ያለሽ እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ በክንድሽ የያዝሺውን (የታቀፍሽውን) መላእክት ያመሰግኑታልና፡፡ እሳታውያን የኾኑ ሱራፌልም ሳያቋርጡ ክንፋቸወን ዘርግተው፡- “የክብር ባለቤት ይህ ነው” ይላሉ፡፡ “በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት የሰውን ኹሉ ኃጢአት ለማስተሥረይ ሰው የኾነ የክብር ባለቤት ይህ ነው” እያሉ በፍርሐት በረዐድ ኾነው ያመሰግኑታል፡፡ የሰውን ኃጢአት በቸርነቱ ብዛት ከሚያሰተሠርይ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

ይህን ሲጨርስ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ባርካው ታርጋለች፡፡ እርሱም ተባርኮ እጅ ነሥቶ ይቀራል፡፡

አነሣሥቶ ላስጀመረን ፤ አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን።

@Ethiopian_Orthodox @Ethiopian_Orthodox

የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡

@Ethiopian_Orthodox

፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛ ሳሙ.፲፮፡፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡

ሙሴ ያየው ሐመልማል ነበልባሉን እንዳላጠፋው ኹሉ ጌታም ምንም እንኳን ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽም ነፍስ ነሥቶ ቢዋሐድም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ ፡፡ ሙሴ በአምሳለ ሐመልማል ወነበልባል ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

@Ethiopian_Orthodox

፬. አንቲ ውእቱ ገራኅተ ዘኢተዘርዐ ውስቴታ ዘርዕ - ዘር ያልወደቀባት፣ ገበሬ ያልጣረባት ያልጋረባት፣ ለታብቁል (ታብቅል) ባለው ቃል ብቻ ከልምላሜ፣ ከጽጌ (ከአበባ)፣ ከፍሬ የተገኘች ገራኅተ ሠሉስ (የማክሰኞ እርሻ) አንቺ ነሽ፡፡ የወንድ ዘር ሳይወድቅብሽ ፍሬ ሕይወት (የሕይወት መገኛ) ጌታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ካንቺ ተወልዷልና፡፡ አረጋዊው ዮሴፍ በትሩፋተ ደሙ የዋጀሽ /ቅዳ.ማር. ቁ. ፻፳፰/፣ ዕንቁ የተባለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ያገኘብሽ /ሃይ.አበ.፺፮፡፶፭/ የተቈለፈች ሣጥን አንቺ ነሽ፡፡ በዚህ አለ፣ በዚያ የለም የማይሉት ሙሉዕ በኵለሄ የኾነ አካላዊ ቃል በማኅፀንሽ አደረ /መዝ.፻፴፱፡፰/፤ በዚህ ዓለምም ማኅተመ ድንግልናሽ እንደተቈለፈ ወለድሽው /ሕዝ.፵፬፡፩-፪/፡፡ በዕንቁ ከተመሰለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፭. ሥጋዌውን ተልከው ለነቢያት ሲነግሩ የነበሩ፣ አሁን ደግሞ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ አይተውት “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር” ብለው በደስታ ያመሰገኑትን ጌታን የወለድሽው ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡

የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽሕት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡- “ኦ ድንግል አምሳል ወትነቢት ዘነቢያት- ነቢያት ትንቢት የተናገሩልሽ ምሳሌ የመሰሉልሽ…” ይላታል /ቅ.ማር.ቁ.፴፯/፡፡ እግዚአብሔር ከነፍስሽ ነፍስ ከሥጋሽ ሥጋ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ኾኗልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን  አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ የሰው ኹሉ ደስታ የሚኾን የመልአኩን ቃል እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ /ዮሐ.፫፡፬-፱/ እንደ ዘካርያስም ሳትጠራጠሪ /ሉቃ.፩፡፳/ አምነሻልና ደስ ይበልሽ /ሉቃ.፩፡፵፭/፡፡ ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታ የወለድሽው ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡

፮. በእውነት ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም በሚገባ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡- “ብልህ ሸክላ ሠሪ የሚሠራውን የለዘበ ጭቃ በአገኘ ጊዜ ከእርሱ መልካም ዕቃ እንዲሠራ፤ እንደዚህም ጌታችን የዚህችን ድንግል ንጹሕ ሥጋዋን ንጽሕት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ሥጋ ሊዋሐደው ፈጠረ” /ሃይ.አበ.፷፮፡፲፬/ እንዲል በቅተሸ ብትገኚ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡

የሔዋን ደኅንነቷ ሆይ! ደስ ይበለሽ፡፡ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግም እንዲህ ይላል፡- “የሕዝቦች ሴቶች ልጆች ሆይ! ከአባቶቻችሁ ስሕተት ነጻ ያወጣችሁን ቅረቡት፤ እርሱንም ማመስገን ተማሩ፡፡ ያ ሔዋን የዘጋችውን የማይናገር አፍ አሁን በእመቤታችን ማርያም ተከፍቷልና ለእኅታችሁ ምስጋናን ለመዘመር ቅረቡ፡፡ አሮጊቷ ሴት (ሔዋን) በምላሶቻችሁ ዙርያ የዝምታን ገመድ ቋጠረች፤ የድንግል ልጅ ግን ጮኻችሁ ታመሰግኑ ዘንድ እሥራታችሁን ፈታ…” /A Metrical Homily on Holy Ephrem, pp 47/፡፡ ከአባቶች አንዱም፡- “እንግዲህስ ሴቶች ኹሉ ሐሴት ያድርጉ፤ አሁን ሴቲቱ ዕፀ በለስን ሳይኾን ዕፀ ሕይወትን አስገኝታለችና፡፡ ዳግመኛም ደናግላን እናቶች ኹሉ በፌሽታ ይዝለሉ፤ ያለመታዘዝን ዕፅ በሴት ተፈውሷልና፡፡ እነሆ ክብሩ ከመላእክት ይልቅ የከበረ ኾኗልና ከእንግዲህ ወዲህ የሴትነት ጾታ የሞትና የውድቀት ምልክት መኾኑ ቀርቷል፡፡ ሔዋን ተፈወሰች፤ ድንግል ግን ከበረች፡፡ እነሆ ድንግሊቱ እናትም አገልጋይም፣ ደመናም ድንኳንም፣ ደግሞም የጌታ ታቦት ኾናለችና፡፡ እንግዲያውስ ኑ! አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ፤ የሔዋን መድኃኒቷ አንቺ ብቻ ነሽ፤ ዓለምን በደሙ የሚገዛትን ጌታ ያስገኘሽ አንቺ ብቻ ነሽ እያልን እናወድሳት” ብሏል፡፡

ፍጥረትን ኹሉ በፀሐይ አብስሎ በዝናብም አብቅሎ የሚመግበውን እርሱ ጡትሽን ይዘሽ አጥተሸዋልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም ለመንፈሳውያን ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበውን እርሱን ጡትሽን ይዘሽ አጥብተሸዋልና ደስ ይበልሽ፡፡

ተጠምቀው ሕያዋን ኾነው የሚኖሩበት ማየ ገቦ ከአንቺ ከተገኘ ከጌታ የተገኘ ነውና የሕያዋን የጻድቃን እናታቸው ንእድ ክብርት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ መቅድመ ተአምርም፡- “ሕይወትየ ይቤላ አዳም ለብእሲቱ አእሚሮ ከመ ትወጽእ እግዝእትነ ማርያም እምሐቌሁ ወእምከርሠ ብእሲቱ - አዳምም እመቤታችን ማርያም ከሱ አብራክ እንድትከፈል ከሔዋንም ማኅፀን እንድትወለድ ዐውቆ ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር” ይላል /መቅድመ ተአምር ቁ. ፲/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም፡- “አዳም ያለ ሩካቤ ድንግል የኾነች ሔዋንን አስገኘ፤ የሕይወት እናት ብሎም ጠራት፡፡ በዚህም ነቢይ ኾነ፤ በኹለተኛ ልደት ከእርሷ የሚያበራ ሕይወት ይገለጣልና፤ በድንግልናዋም የእግዚአብሔር ልጅን ታስገኛለችና፡፡ በአዳም ትንቢት የእውነት ሕይወት የኾነው የጌታችንን መምጣት በምሳሌ ተናገረ፡፡ እናቱም ድንግል ማርያም ኾነች፡፡ ሔዋንን የሕያዋን ኹሉ እናት ብሎ ጠራት፤ ሕይወትን አስገኝታለችና፡፡ እርሱም ኢየሱስ የተባለው ጌታችን ነው” ይላል /Jacob of Serug, On the Virgin, pp 36/፡፡ አንድም “ነዋ ወልድኪ- እነሆ ልጅሽ” /ዮሐ.፲፱፡፳፮/ ባለ ጊዜ በዮሐንስ እኛን ለእርሷ መስጠቱ ነውና የሕያዋን ኹሉ እናታቸው ንዕድ ክብርት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ለምኚልንና ትልምኝልን ዘንድ ዓይነ ሕሊናችንን ወደ አንቺ እንሰቅላለን፡፡

፯. ድንግል ሆይ! ንዕድ ክብርት ሆይ! ጌታን የወለድሽው ሆይ! እኛን ለማዳን ድንቅ የሚያሰኝ ተዋሕዶ በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን ወለድሽልን፤ መንክር በአርያሙ የሚባል ጌታ በማኅፀንሽ አደረ፡፡ ነገር ግን በብዙ ኅብረ መልክእ፣ በብዙ ፆታ መልክእ ሃያ ኹለቱን ሥነ ፍጥረት የፈጠረ፣ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን በብዙ ፆታ በብዙ ዕድል እንደየ ሰዉ የአእምሮ ስፋት የሃይማኖት ጽናት የሚያድል፣ ልዕልናውን ገናንነቱን በብዙ መንክር ራዕይ በብዙ ወገን (ለምሳሌ በፀሐይ፣ በቀላይ፣ …) የተመሰለ እርሱን የጌትነቱን ነገር ጠንቅቀን (ፈጽመን) መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል፡፡ ዳግመኛም በብዙ ኅብረ ትንቢት (ለምሳሌ ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ተብሎ) የተነገረ፣ በብዙ ኅብረ አምሳል (ለምሳሌ በአምሳለ ነበልባል ወሐመልማል፣ በአምሳለ ጠል ወፀምር፣ በአምሳለ አንበሳ፣ በአምሳለ እብን ቅውም) የተመሰለ የርሱን የሥጋዌውን ነገር ጠንቅቀን (ፈጽመን) መናገር አይቻለንምና ናርምም (ዝም እንበል)፡፡

ሥጋዌው በአምሳለ ነበልባል ወሐመልማል፣ በአምሳለ ጠል ወፀምር ከተመሰለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

@Ethiopian_Orthodox ፯. ወደ ደብረ ሲና የወረደው፣ ለሙሴ ሕገ ኦሪትን የሠራ፣ የተራራውን ራስ በጨለማ በእሳት በጽጋግ በነፋስ (በዕበየ ግርማው)  የሸፈነ፣ ፈርተው የቆሙትን ፈጥኖ በሚሰማ በረቂቅ ነጋሪት ድምጽ የገሠፀ እርሱ የሰው ልጆችን ለማዳን ፭ ሺሕ ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ሰው ኾኖ የመጣው የአብ አካላዊ ቃል ነው፡፡ በሌላ አንቀጽም ይኸው ሊቅ፡- “እም ደብረ ሲና ወፅአ እሳት ወጽልመት ወእምኔኪ ወፅአ ለነ አምላክ ወሰብእ፡፡ እም ደብረ ሲና ወፅአ ድንጋፄ ወሀውከ ላዕለ አይሁድ ወእምኔኪ ወፅአ ሁከት ወድንጋፄ ዐቢይ ላዕለ አይሁድ ወሄሮድስ ወዲያብሎስ ምስለ አጋንንቲሁ - ከደብረ ሲና እሳት ጨለማ ወጣ፤ ከአንቺ ግን ሰው የኾነ አምላክ ተገኘልን፡፡ በደብረ ሲና በአይሁድ ላይ ድንጋፄ ሀውክ ተደረገ፤ በአንቺም በአይሁድ በሄሮድስ በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ ጽኑ ድንጋፄ ተደረገ” ብሏል /ዘጸ.፳፡፲፰፣ ዕብ.፲፪፡፲፱፣ ሃይ.አበ.፵፯፡፱-፲/፡፡ እንዲህ ከተባለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፰. “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ” ከሚለው የኢሳይያስ አንቀጽ /ኢሳ.፯፡፲፬/ ስትደርሺ “እኔ በኾንኩኝ” ሳትዪ፤ ይልቁንም “ምነው ከዘመኗ ደርሼ፣ ወጥቼ ወርጄ በድንግልና የምትወልደውን ድንግል ባገለገልኳት” ብለሽ በትሕትና የተናገርሽ ደብር ነባቢት ሆይ! ሰውን የሚወድ፣ ሰውም የሚወደው ጌታ ባሕርዩ ሳይለወጥ ካንቺ ከሥጋሸ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ እንደኛ የሚናገር ሥጋን ነሥቶም ሰው ኾነ፡፡ ጥበብን በሚገልጽ፣ ሥጋዌን በሚያስፈጽም በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክ በማኅፀንዋ አደረና ፍጹም ሰው ኾነ፡፡ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት አዳምን ያድነው ዘንድ፣ ኃጢአቱንም ያስተሠርይለት ዘንድ፣ በሰማያዊ ቦታ በሰማያዊ መዓርግ ያኖረው ዘንድ /ኤፌ.፪፡፮/፣ ወደ ቀደመው ቦታው ወደ ቀደመው ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ፍጹም ሰው ኾነ፡፡ በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት አዳምን ወደ ቀደመው ቦታ ከመለሰው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፱. የድንግል ክብሯ ሊናገሩት አይቻልም፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ይኸው እየተናርን አይደለምን?” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- “ለርሷ እንደሚገባ አድርጎ መናገር የሚቻለው የለም” ሲል ነው፡፡ “ለምን?” ጌታ መርጧታልና፡፡ አሁንም ከእናንተ መካከል፡- “ታድያ እርሱ ከመረጣትማ ምን ይደንቃል?” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ፡ “በአማን ነጸረ እግዚአብሔር አብ እምሰማይ ምሥራቀ ወምዕራበ ሰሜነ ወደቡበ ወውስተ ኵሉ አጽናፍ አስተንፈሰ ወአጼነወ ወኢረከበ ከማኪ ወሠምረ መዐዛ ዚአኪ ወአፍቀረ ሥነኪ ወፈነወ ኀቤኪ ወልዶ ዘያፈቅር - እግዚአብሔር አብ በሰማይ ኾኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንንና ደቡብን ዳርቻዎችን ኹሉ በእውነት ተመለከተ፤ ተነፈሰ፤ አሻተተም፤ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፡፡ የአንቺ መዐዛ ወደደ፤ የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ላከ” ብሎ እንደተናገረው እንድትመረጥ ኾና ተገኝታለችና ነው /ቅዳ.ማር.ቁ.፳፬/፡፡

ሐዋርያው “ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል” እንዲል /፩ኛ ጢሞ.፮፡፲፮/ በመመርመር ገንዘብ በማድረግ የሚቀርበው በሌለው ብርሃን ባሕርዩ አድሮ የሚኖረ እርሱ /ሃይ.አበ.፴፫፡፫/ ሰው ኾኖ በማኅፀንዋ አደረ /ዮሐ.፩፡፲፬/፡፡ ዘጠኝ ወር ከአምስተ ቀን በማኅጸንዋ ኖረ፡፡ ሰውም ከመኾኑ አስቀድሞ ሰውም ከኾነ በኋላ የማይመረመር እርሱን ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው፡፡ ሰውም ከመኾኑ አስቀድሞ ሰውም ከኾነ በኋላ ከማይመረመረው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፲. ነቢዩ ዳንኤል ያየውና እጅ ሳይፈነቅለው ከረጅም ተራራ የወረደው ደንጊያ /ዳን.፬፡፩-፴፭/ ከአብ ዘንድ የወጣው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ያ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ከረዥሙ ተራራ እንደተፈነቀለ ኹሉ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ዘር ምክንያት ሳይኾነው ከድንግል ተወለደ፡፡ ዳንኤል በአምሳለ እብን (ደንጊያ) ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፲፩. ሐሩረ ፀሓይ ያልወደቀባት፣ ነፋስ ያልወዘወዛት፣ ለታብቁል (ታብቅል) ባለው ቃል ከልምላሜ፣ ከጽጌ፣ ከፍሬ የተገኘች ዐፅቀ ሠሉስ (የማክሰኞ ቅርንጫፍ) አንች ነሸ /ኩፋ.፪፡፲፪/፡፡ እንዲህ ማለቱ ነው፡- “በዕለተ ሠሉስ የተገኙ ቅጠሎች፣ ቅርንጫፎች ፀሐይ እንዳላጠወለጋቸው፣ ነፋስ እንዳልወዘወዛቸው ኹሉ አንቺም የኃጢአት ፀሐይ አልለወጠሽም፡፡ በሥጋሽ፣ በነፍስሽ፣ በኅሊናሽም ድንግል ነሽ እንጂ” /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን፣ ክፍል ፩፣ ገጽ ፲/፡፡ አባ ጊዮርጊሥም፡- “በበደል ምሣር የማትቈረጪ፣ ከኀጢአት ዐውሎ ነፋስ የተነሣ የማትነዋወጪ፣ ዘወትር ፍጹም የምትለመልሚ፣ በዘመኑ ኹሉ የምታፈሪ፣ በወሮች ኹሉ የምትለቀሚ፣ ከዕፅዋት ኹሉ ይልቅ የምታምሪ እመቤቴ ማርያም ሆይ! የተባረክሽ ዕፅ ነሽ” ይላታል /እንዚራ ስብሐት፣ ገጽ ፲፬/፡፡ አምላክን የወለድሽ ንጽሕት፣ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ኅትምት የምትኾኝ ሆይ! ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ስለ ማዳን ሰው ኹኗልና (አካላዊ ቃልን ወልደሽልናልና) የሃይማኖትም (የክርስቶስም) ሙዳይ (መገኛ) ነሽ፡፡ (በልጅሽ ላመኑ) የአባቶቻችን የቀናች ሃይማኖታቸው ነሽ፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፲፪. የከበርሽ አምላክን የወለድሽ ሆይ! የማይመረመር ቃልን የወሰንሺው የብርሃን እናቱ አንች ነሽ፡፡ እርሱንም ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኖረሻልና በአፍኣ በውስጥ በሥጋ በነፍስ ያከብሩሻል፤ ያገኑሻል፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

@Ethiopian_Orthodox

፲፫. ወዮ! ስለ አንቺ ድንቅ ኾኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? ቅድመ ዓለም ያለ እናት ተወልዶ፣ ድኅረ ዓለም ያለ አባት እንደምን እንደወለደሽው መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? የአካላዊ ቃል እናቱ ንጽሕት ደንግል ሆይ! ኪሩቤል ለሚሸከሙት ለንጉሥ ማደሪያ ኾንሽ፡፡ ንዕድ ክብርት ሆይ! እኛም ክብርሽን ገናንነትሽን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እናመሰግንሻለን /ሉቃ.፩፡፵፰/፡፡ የአካላዊ ቃል እናቱ መልካሟ ርግብ (ርግበ ኖኅ) ማርያም ሆይ! ስምሽን በትውልደ ሴም፣ በትውልደ ካም፣ በትውልደ ያፌት እንጠራለን፡፡ ሊቁ እመ አምላክን “መልካሟ ርግብ” አላት፡፡ ይኸውም የኖኅ ርግብ “የጥፋት ውሃ ጐደለ፤ የጥፋት ውሃ ተገታ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰላም ነው” ስትል የምሥራቹን የዘይት ቅጠል ይዛ እንደታየች ኹሉ /ዘፍ.፰፡፲፩/ እመቤታችንም “የኀጢአት ውሃ ጐደለ፤ የመርገም ውሃ ተገታ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዘመነ ሰላም ነው” ስትል ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔን ኣሳልፎ ዓመተ ምሕረትን የተካ፣ ለዓለሙ ኹሉ ታላቅ የምሥራች የኾነ፣ የዓለም መድኃኒት ክርስቶስን ወልዳልናለችና፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

---------------Closed/Hired---------------

Job Title: Legal Counsel - Real Estate & Hospitality Regulatory

Company: Private Client View Rate:🟢 80%-100% Excellent

Salary: 15,000 ETB - 30,000 ETB

Deadline: 14-08-2026

Description: About the Role: We are building a technology platform in the property rental space, launching in Addis Ababa. We are seeking a local lawyer to provide guidance as we establish the legal and regulatory framework for our business prior to launch. This is a consulting engagement (retainer) with the potential to evolve into an ongoing advisory relationship as the company expands.

What You'll Help Us With: • Business registration and structuring (including considerations around foreign investment participation) • Navigating the regulatory landscape for property rental services in Addis Ababa, including the new municipal lodging tax and registration requirements • Drafting host/property-owner agreements and standard terms of service • Providing guidance on liability, insurance, and dispute resolution frameworks between the platform, hosts, and guests • Ensuring payments and tax compliance (VAT, municipal levies, foreign currency considerations) • Conducting general regulatory risk assessments as we scale beyond an initial pilot

Who We're Looking For: • Ethiopian-qualified lawyer based in Addis Ababa • Strong background in real estate, property, or hospitality law; regulatory/compliance experience is a significant plus • Familiarity with Ethiopian investment law and business licensing processes • Comfortable advising an early-stage startup; pragmatic, responsive, and able to work directly with founders rather than through a large firm process • Fluent in Amharic and English

Engagement: • Initial scope: a working session to map out the regulatory landscape, followed by ongoing advisory support • Open to remote consultations with in-person meetings as necessary

Please Note: Further business details will be shared under a mutual NDA before any engagement begins.

To Apply: Send a brief note outlining your relevant experience along with your rate structure to @N07m3p on Telegram.

Share this Job↗️ Reviewed & Approved by Maroset

Join our Socials: LinkedIn || YouTube || TikTok || Facebook || Telegram

Aug 11, 05:44 AMMore from @maroset

#New Vacancy at Federal Civil Service Commission /የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

✅የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት 3 ተቋማት ክፍት የሥራ ቦታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ ከታች በተቀመጠው የያንዳንዱ ሊንክ በመጫን Online ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 ለኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጽሕፍት አገልግሎት ሊንከ

 ለኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም

 ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት

📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇 👉Read Detail:- https://ethioworks.com/ethiopian-civil-service-commission-job-vacancy/

📌ዛሬ የወጡ የስራ ማስታወቂያዎች በአንድ ቦታ በዚህ ሊንክ ዌብሳይቱ ላይ ይመልከቱት👇👇👉 www.harmeejobs.com

🎓Telegram:- https://t.me/harmeejobs

Aug 11, 04:47 AMMore from @harmeenews

በኢትዮጵያ የወረቀትና የሕትመት ቁሳቁስ ዋጋ መናር እና የከፍተኛ ግብር ጫና የመጻሕፍት ዘርፉን አደጋ ላይ መጣላቸው ተገለጸ።

የኤዞፕ መጽሐፍ መደብር ባለቤት አቶ መለሰ ማሩ እንዳሉት፤ የካፒታልና የምርት ወጪ መጨመር የአንድ መጽሐፍ መነሻ ዋጋ እስከ 1,000 ብር እንዲደርስ በማድረጉ ደራሲያንና አንባቢዎች ከዘርፉ እያራቀ ነው።

በተጨማሪም የመድረክና ኤግዚቢሽን ማዘጋጃ ወጪዎች መወደድና የትልልቅ ተቋማት የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ እጥረት ችግሩን ያባበሰው ሲሆን፣ ሁኔታው በጥቂት ወገኖች ጥረት ብቻ ሊፈታ እንደማይችል ጠቅሰዋል።

የችግሩ ዋና መንስኤዎች ካሏቸው መካከል የ15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የግብር ጫና፣ ሙሉ በሙሉ ከውጭ የሚገቡ የሕትመት ጥሬ ዕቃዎች ዋጋ መናር እና የስፖንሰርሺፕ እጥረት አንዱ ሲሆን።

በዚህም የአንድ መጽሐፍ መነሻ ዋጋ እስከ 1,000 ብር ማደግ ደራሲያንንና አንባቢዎችን ከዘርፉ አራርቋል፤ የመጻሕፍት ኤግዚቢሽኖችና የምረቃ መድረኮችን ለማዘጋጀትም አስቸጋሪ አድርጎታል ተብሏል፡፡ የኤዞፕ መጽሐፍ መደብር ባለቤት አቶ መለሰ ማሩ ችግሩ በትልልቅ ተቋማት (እንደ ባንኮች) ድጋፍ ባለመታገዙ የከፋ መሆኑን ጠቁመው፣ በጥቂት አታሚዎችና ደራሲያን ጥረት ብቻ ሊፈታ እንደማይችል ገልጸዋል።

Source: Ethio FM 107.8 @Ethiopianbusinessdaily